Monday, February 13, 2012

የሳምንቱ ጥቅስ

__የዮሐንስ፡ራእይ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13፤
1፤አንድም፡አውሬ፡ከባሕር፡ሲወጣ፡አየኹ፤ዐሥር፡ቀንዶችና፡ሰባት፡ራሶች፡ነበሩት፥በቀንዶቹም፡ላይ፡ዐሥር፡ዘ ውዶች፡በራሶቹም፡ላይ፡የስድብ፡ስም፡ነበረ።
2፤ያየኹትም፡አውሬ፡ነብር፡ይመስል፡ነበር፥እግሮቹም፡እንደ፡ድብ፡እግሮች፥አፉም፡እንደ፡አንበሳ፡አፍ፡ነበሩ ።ዘንዶውም፡ኀይሉንና፡ዙፋኑን፡ትልቅም፡ሥልጣን፡ሰጠው።
3፤ከራሶቹም፡ለሞት፡እንደ፡ታረደ፡ኾኖ፡አንዱን፡አየኹ፥ለሞቱ፡የኾነውም፡ቍስል፡ተፈወሰ።ምድርም፡ዅሉ፡አውሬ ውን፡እየተከተለ፡ተደነቀ፥
4፤ለዘንዶውም፡ሰገዱለት፥ለአውሬው፡ሥልጣንን፡ሰጥቶታልና፤ለአውሬውም፦አውሬውን፡ማን፡ይመስለዋል፥ርሱንስ፡ ሊዋጋ፡ማን፡ይችላል፧እያሉ፡ሰገዱለት።
5፤ታላቅንም፡ነገርና፡ስድብን፡የሚናገርበት፡አፍ፡ተሰጠው፥ባርባ፡ኹለት፡ወርም፡እንዲሠራ፡ሥልጣን፡ተሰጠው።
6፤እግዚአብሔርንም፡ለመሳደብ፡ስሙንና፡ማደሪያውንም፡በሰማይም፡የሚያድሩትን፡ሊሳደብ፡አፉን፡ከፈተ።
7፤ቅዱሳንንም፡ይዋጋ፡ዘንድ፡ድልም፡ያደርጋቸው፡ዘንድ፡ተሰጠው፥በነገድና፡በወገንም፡በቋንቋም፡በሕዝብም፡ዅ ሉ፡ላይ፡ሥልጣን፡ተሰጠው።
8፤ከዓለምም፡ፍጥረት፡ዠምሮ፡በታረደው፡በግ፡ሕይወት፡መጽሐፍ፡ስሞቻቸው፡ያልተጻፉ፡በምድር፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ይ ሰግዱለታል።
9፤ዦሮ፡ያለው፡ቢኖር፡ይስማ።
10፤ይማረክ፡ዘንድ፡ያለው፡ማንም፡ቢኖር፡ወደ፡ምርኮነት፡ይኼዳል፤በሰይፍ፡የሚገድል፡ማንም፡ቢኖር፡ራሱ፡በሰ ይፍ፡እንዲገደል፡ይገ፟ባ፟ዋል።የቅዱሳን፡ትዕግሥትና፡እምነት፡በዚህ፡ነው።
11፤ሌላም፡አውሬ፡ከምድር፡ሲወጣ፡አየኹ፥የበግ፡ቀንዶችን፡የሚመስሉ፡ኹለት፡ቀንዶችም፡ነበሩት፡እንደ፡ዘንዶ ም፡ይናገር፡ነበር።
12፤በፊተኛውም፡አውሬ፡ሥልጣን፡በርሱ፡ፊት፡ዅሉን፡ያደርጋል።ለሞቱ፡የኾነውም፡ቍስል፡ተፈወሰለት፡ለፊተኛው ፡አውሬ፡ምድርና፡በርሱ፡የሚኖሩት፡እንዲሰግዱለት፡ያደርጋል።
13፤እሳትንም፡እንኳ፡ከሰማይ፡ወደ፡ምድር፡በሰው፡ፊት፡እስኪያወርድ፡ድረስ፡ታላላቆችን፡ምልክቶች፡ያደርጋል ።
14፤በአውሬውም፡ፊት፡ያደርግ፡ዘንድ፡ከተሰጡት፡ምልክቶች፡የተነሣ፡በምድር፡የሚኖሩትን፡ያስታል፤የሰይፍም፡ ቍስል፡ለነበረውና፡በሕይወት፡ለኖረው፡ለአውሬው፡ምስልን፡እንዲያደርጉ፡በምድር፡የሚኖሩትን፡ይናገራል።
15፤የአውሬው፡ምስል፡ሊናገር፡እንኳ፡ለአውሬውም፡ምስል፡የማይሰግዱለትን፡ዅሉ፡ሊያስገድላቸው፥ለአውሬው፡ም ስል፡ትንፋሽ፡እንዲሰጠው፡ተሰጠው።
16፤ታናናሾችና፡ታላላቆችም፡ባለጠጋዎችና፡ድኻዎችም፡ጌታዎችና፡ባሪያዎችም፡ዅሉ፡በቀኝ፡እጃቸው፡ወይም፡በግ ንባራቸው፡ምልክትን፡እንዲቀበሉ፥
17፤የአውሬውም፡ስም፡ወይም፡የስሙ፡ቍጥር፡ያለው፡ምልክት፡የሌለበት፡ማንም፡ሊገዛ፡ወይም፡ሊሸጥ፡እንዳይችል ፡ያደርጋል።ጥበብ፡በዚህ፡አለ።
18፤አእምሮ፡ያለው፡የአውሬውን፡ቍጥር፡ይቍጠረው፤ቍጥሩ፡የሰው፡ቍጥር፡ነውና፥ቍጥሩም፡ስድስት፡መቶ፡ስድሳ፡ ስድስት፡ነው።

No comments:

Post a Comment

በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮህኩ።

ትንቢተ ዮናስ 2÷1-እስከመጨረሻው እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ። ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ...