Wednesday, April 29, 2020

በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮህኩ።

ትንቢተ ዮናስ 2÷1-እስከመጨረሻው

እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።
ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦
በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ።
እኔም፦ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ።ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር። ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስ ገባች።ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።

ደጉ ሳምራዊ



ሉቃስ 10 ÷30-36
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ። እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ።አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፦ ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው። እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?


Monday, April 27, 2020

ፈላስፋ

በምንሰራው ሥራ ሁሉ ረዳታችን አጋዣችንን አዛኝ ይቅር ባይ በሚሆን በእግዚአብሔር ስም የፈላስፎችን አነጋገር መጻፍ እንጀምራለን።
ፈላስፋ ማለት ጥበበኞች ወይም የእውቀት ሰዎች ማለት ነው።
ከሰነፍ ሽማግሌ ብልህና አስተዋይ ወጣት ይሻላል።ጥበብና ተግሳጽ ተርታውን ሰው  ታላላቆች ሰዎች ከደረሱበት ደረጃ ያደርሱታል።ከትልቅ ሰው የተወለደውን ከተራ ሰው የተወለደውን ሳይለዩ ያከብራሉ ያስከብራሉ።
"ከትንሽ ወይም ከትልቅ መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለትልቅ ክብር መውለድ ግን ሙያ ነው" ቀ.ኃ.ሥ

ምንጭ፡አንጋረ ፈላስፋ

ነገረ ፈላስፋ

ይዘጋጃል.....

Sunday, April 26, 2020

በመድኃኒቱ ያድናቸዋል በሽታቸውንም

«እግዚአብሔር መድኃኒትን ከምድር ፈጥሯልና አዋቂ ሰው ባለ መድኃኒትን አይንቀውም። ታምራቱን ያወቁ ዘንድ ውሃ በእንጨት የጣፈጠ አይደለምን? በታምራቱ ይከበሩ ዘንድ እግዚአብሔር ለሰዎች ጥበብን ሰጣቸው። በመድኃኒቱ ያድናቸዋል በሽታቸውንም ያርቅላቸዋል። በሚያድኑ ገንዘብ ከነሳቸው መድኃኒት ያደርጋሉ እሱም ለሀገር ፍቅርን ያመጣል።» ፴፰፡፬-፰።

መጽሐፍ ሲራክ

መጽሐፈ ሲራክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ከብሉይ መጻሕፍት የሚመደብ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ

 የኢትዮጵያ ትርጓሜ መጻሕፍት ጥበብ ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ትምህርት በኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የራቀውን አቅርባ የረቀቀውን አግዝፋ፣ የ ቀጨጨውን አወፍራ የምታቀርብበት የመጻሕፍት ምስጢር መተንተኛ ሥልት አላት፡ ፡ ይህ ስልት መጻሕፍት  ቤት በተባለው ጥንታዊ የ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ደረጃ የሚሰጠውና አንድምታ ተብሎ የሚታወቀው ትምህርት ነው፡ ፡ 

በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮህኩ።

ትንቢተ ዮናስ 2÷1-እስከመጨረሻው እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ። ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ...